Elementor #11675

የዉኃ ፓንፖችን ከርቀት መቆጣጠር የሚያስችል ስካዳ ሲስተም በከፊል ስራ ጀመረ፡፡

ባህርዳር፤ መጋቢት 19 / 2017 የባህ/ዉ/ፍ/አገ/

የባህር ዳር ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ከ4 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጅ ኦፍ ኢንስቲትዩት ሲያለማ የነበረዉን ፓንፖችን ከርቀት መቆጣጠር የሚያስችል የስካዳ ሲስተም ቴክኖሎጅ በስምንት ያህል ፓንፖች የትግበራ ስራዉን ጀምሯል፡፡

ቴክኖሎጅዉ እስከ 25 ኪሎ ሜትር ድረስ በርቀት የሚገኙ 17 ያህል ፓንፖችን ዋና ቢሮ ላይ ቁጭ ብሎ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ እየሠሩ ያሉና ያልሰሩ ፓንፖችን በመለየት የዉኃ ምርት ሳይቋረጥ እንዲጨምር ከማድረጉ በተጨማሪ በኤሌክትሪክ ኃይል መዋዠቅ ምክንያት ችግሮች ሲኖሩ አስቀድሞ የማንቂያ መልእክቶችን የሚልክና የሚያሳይ በመሆኑ ሊቃጠሉ የሚችሉ ፓንፖችን ማዳን ያስችላል፡፡

አሁን ላይ ስራዉን እንዲቆጣጠሩ አራት ያህል ባለሞያዎች ተበድበዉ አስፈላጊዉን ስልጠና በመዉሰድ በፈረቃ እየሰሩ ይገኛል፡፡

ቴክኖሎጅዉ በእነዚህ ፓንፖች እየሰራ ከቆየ በኋላ ጎን ለጎን ለባለሙያዎች ስልጠናዎቹን በማጠናከር በሌሎች ቀሪ ዘጠኝ ፓንፖች ላይ ተገጥሞ በቀጣይ ጊዜያት ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባ ይሆናል፡

Leave A Comment

Categories

Recent News

Elementor #11675

29 መጋቢ 2025

Elementor #11670

28 መጋቢ 2025

Elementor #11660

28 መጋቢ 2025

Archives