Elementor #11645

የባሕርዳር ከተማ ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት አጠቃላይ ሽፋን 80% መድረሱን የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።

(መጋቢት 13/2017 ባሕርዳር) የባሕርዳር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከውሃና ፍሳሽ ደንበኞች ፎረም ጋር በመተባበር መጋቢት 22 “የበረዶ ግግር ጥበቃ” በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የውሃ ቀንን ምክንያት በማድረግ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር በውሃ አቅርቦትና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ተደራሽነት እንዲሁም ስኬቶችና ጉድለቶች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
የባሕርዳር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይርጋ አለሙ በምክክር መድረኩ መክፈቻ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልካም ምኞት መልዕክታቸውን በማስቀደም የ33ኛውን የዓለም የውሃ ቀንን ምክንያት በማድረግ በውሃና አፍሳሽ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የተመዘገቡ ስኬቶችንና የሚገጥሙ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመገምገም እና በመመካከር ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ተደራሽነት ለሁሉም በሁሉም እውን እንዲሆን በጋራ ለመስራት ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል።
በተለይም የባሕርዳርን ስማርት ሲቲ እውን ለማድረግ የሚከናወኑ የኮሪደር ልማትና ሌሎች የመሰረተ ልማት ስራዎችን ተከትሎ የንፁህ መጠጥ ውሃ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ተግባራትንም አያይዞ በማልማት በኩል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው በዚህም የውሃና ፍሳሽ ደንበኞች ፎረም እንዲሁም መላ ማህበረሰቡ ከድርጅቱ ጎን በመሆን ስኬታማ የሆነ አገልግሎት መስጠት እንዲቻል ተፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የባሕርዳር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የህዝብ ግንኙነትና የደንበኞች አገልግሎት ስራ ሂደት መሪ አቶ ደስታ አንለይ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን እንደ ባሕርዳር ከተማ በገጠር ፣በሳተላይትና በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች አጠቃላይ ከ596,524 በላይ ህዝብ እንደሚኖር በመጥቀስ አገልግሎት ድርጅቱ ለዚህ ህዝብ በ35 የውሃ ማሰራጫ ተቋማት 13 ሚሊዮን ሜትር ኪዩቭ ውሃ ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በ2017 በጀት ዓመት 30 ሚሊዮን ሜትር ኪዩቭ ውሃ ለማቅረብ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን በዚህም እሰከ አሁን ባለው አፈፃፀም 15 ሚሊዮን ሜትር ኪዩቭ ውሃ ማቅረብ መቻሉን እንዲሁም ከነባሩ የውሃ መስመር በተጨማሪ የህዝብ ብዛትና የፍላጎት እድገትን መሰረት በማድረግ 124.68 ኪሎ ሜትር አዳዲስ የውሃ ዝርጋታ መስመሮችን ተደራሽ ማድረጋቸውንና የውሃ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ስራ ሽፋን 82.12% መድረሱን ተናግረዋል።
በአጠቃላይ እስካሁን ያለው የባሕርዳር ከተማ የውሃ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ሽፋን በማሳደግ በኩል የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች በመለየት ለመፍታት ጥረት እየተደረገ መሆኑንና የደንበኞችን እርካታ በመጨመር በኩል የሞባይል ባንኪንግ ተጠቅመው ያለምንም እንግልት የወርሃዊ ፍጆታ ክፍያቸውን ባሉበት እንዲከፍሉ ከባንኮች ጋር የማስተሳሰር ተግባር መሰራቱንም ገልፀዋል።
የባሕርዳር ከተማ ውሃና ፍሳሽ ደንበኞች ፎረም ሰብሳቢ አቶ ክንዴ ይታየው የከተማ አስተዳደሩ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የደንበኞችን እርካታ ያገናዘበ ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት በማመቻቸት ጥራትና ተደራሽነቱ የተረጋገጠ ተግባር እንዲፈፅም መደገፍ ፣የአሰራር ግድፈቶችና መሰል ወንጀሎችን በመከታተል እንዲታረሙ በማድረግ በኩል ተቀናጅቶ የመስራት ቁርጠኝነት በሁሉም ዘንድ ልዩ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።
የባሕርዳር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ም/ስራ አስኪያጅ አቶ በሪሁን አለሙ በውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ዘርፉ የሚስተዋሉ የውሃ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ተደራሽነት እጥረቶች እንዲሁም መሰል የብልሽትና የስርቆት ወንጀሎችን በጋራ በመከላከል በእያንዳንዱ ቤት ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ በማድረግ በከተማችን ምንም ዓይነት የውሃ ፍላጎት እጥረትና ብክለት እንዳይከሰት ሁሉም አጋርና ባለድርሻ የሆነ አካል ባልተቋረጠ ቅንጅት ላይ ተመስርቶ መስራት ዋነኛው መፍትሄ መሆኑን ተናግረዋል።

Leave A Comment

Categories

Recent News

Elementor #11675

29 መጋቢ 2025

Elementor #11670

28 መጋቢ 2025

Elementor #11660

28 መጋቢ 2025

Archives