በደንበኞች በኩል የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ እቅድ አዘጋጅቶ እየሠራ መሆኑን በባህር ዳር ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት የአፄ ቴወድሮስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አሰታወቀ፡፡
በባህር ዳር ከተማ መጠጥ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት የአፄ ቴወድሮስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት የ2ኛ ሩብ አመት እቅድ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር አፈፃፀሙን ከሰራተኞቹ ጋር በገመገመበት ወቅት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳልካቸዉ ግርማ እንዳስታወቁት ቅርንጫፉ በአለፉት ስድስት ወራት በደንበኞች በኩል የነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት እራሱን የቻለ የአገልግሎት አሰጣጥና…