በደንበኞች በኩል የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ እቅድ አዘጋጅቶ እየሠራ መሆኑን በባህር ዳር ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት የአፄ ቴወድሮስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አሰታወቀ፡፡

  • መግቢያ
  • Blog Standard
  • Business
  • በደንበኞች በኩል የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ እቅድ አዘጋጅቶ እየሠራ መሆኑን በባህር ዳር ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት የአፄ ቴወድሮስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አሰታወቀ፡፡
07 መጋቢ, 2025

በደንበኞች በኩል የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ እቅድ አዘጋጅቶ እየሠራ መሆኑን በባህር ዳር ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት የአፄ ቴወድሮስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አሰታወቀ፡፡

በባህር ዳር ከተማ መጠጥ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት የአፄ ቴወድሮስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት የ2ኛ ሩብ አመት እቅድ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አስተዳደር አፈፃፀሙን ከሰራተኞቹ ጋር በገመገመበት ወቅት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳልካቸዉ ግርማ እንዳስታወቁት ቅርንጫፉ በአለፉት ስድስት ወራት በደንበኞች በኩል የነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታት እራሱን የቻለ የአገልግሎት አሰጣጥና የመልካም አሰተዳደር እቅድ ተይዞ ሲሰራ ቆይቷል ፡፡
ከእነዚህ መካከል ቆጣሪ አልተነበበልኝም፤ዉኃ አጣሁ፤ ክፍያ በዛብኝ የሚሉና ሌሎች በርካታ ጥያቄዎችን ቅርንጫፉ ልዩ ልዩ አሰራሮችን በመዘርጋት የመፍታት ስራዎችን እንደሰራ ገልፀዉ ለአብነትም የቆጣሪ ንባብ ችግርን ለመፍታት አንባቢዎችን በአራት ካታጎሪ በመክፈል ማለትም ወሩ በገባ ከ1-5 ፤ ከ5-10 ፤ ከ10-15 ፤ ከ15-20 ባሉ ቀናቶች የትና ማን ቆጣሪ አንባቢ እንደተመደበ ለደንበኞች የማሳወቅ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል፡፡

Leave A Comment