የፍሳሽ ቆሻሻ አገልግሎት

የፍሳሽ ቆሻሻ አገልግሎት

ባህር ዳር ከተማ በአሁኑ ሰአት የተለየ ዘመናዊ የፍሳሽ ዝቃጭ ማከሚያ ጣቢያ ስለሌለው ከከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው “ቆሼ” በሚባል ክፍት ቦታ ላይ እንዲወገድ እየተደረገ ይገኛል። የባህር ዳር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ዘመናዊ የፍሳሽ ዝቃጭ ማከሚያ ጣቢያ ለመገንባት የጨረታ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ ተቋሙ ለፍሳሽ ማንሻ በአንድ የፍሳሽ መኪና እየሰራ ሲሆን፣ የግል ንግድ ድርጅቶች ደግሞ በከተማው ውስጥ ወደ አስር የሚጠጉ ተጨማሪ የፍሳሽ መኪናዎችን አማካኝነት የማስወገድ ስራ ይሰራሉ።

የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና ችግሮችን ለመፍታት እና በየቦታው መጸዳዳትን ለመቀነስ ተቋሙ በባህር ዳር ከተማ ከአንድ መቶ በላይ የህዝብ እና የጋራ መጸዳጃ ቤቶችን ገንብቶ እያስተዳደረ ይገኛል። እነዚህ ውጥኖች በከተማዋ የንፅህና አጠባበቅ አገልግሎትን ለማጎልበት እና የህብረተሰቡን የጤና ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ነው።

Let us help you get your project started.

Contact us
+44(0)20 3156
+1 866 512 0268

Start your project