የባህር ዳር ከተማ መጠጥ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ለቀጣይ አስር አመታት የሚያገለግል መሪ እቅድ

  • መግቢያ
  • Blog Standard
  • Branding
  • የባህር ዳር ከተማ መጠጥ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ለቀጣይ አስር አመታት የሚያገለግል መሪ እቅድ
07 መጋቢ, 2025

የባህር ዳር ከተማ መጠጥ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ለቀጣይ አስር አመታት የሚያገለግል መሪ እቅድ

የባህር ዳር ከተማ መጠጥ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ለቀጣይ አስር አመታት የሚያገለግል መሪ እቅድ በማዘጋጀት ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ባህርዳር፤ ታህሳስ 22 / 2017 ዓ.ም የባህር ዳር ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት
የዉኃ አገልግሎቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ይርጋ አለሙ በተዘጋጀዉ የአስር አመት መሪ እቅድ ረቂቅ ጥናት ዉይይት መድረክ ላይ እንደተናገሩት ተቋሙ ከተቋቋመበት ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ መሪ እቅድ ሳይኖረዉ ለበርካታ አመታት በአመታዊ እቅድ ብቻ ሲመራ ቆይቷል ብለዋል ፡፡
ይህም ተቋሙን ለብዙ ጊዜ የቀን ከቀን (አክቲቭ ቤዝድ) ስራዎች ላይ ብቻ ተመስርቶ እዲሰራና የሰዉ ሃብቱንና ንብረቱን በሙሉ አቅም ተጠቅሞ ወደ ፊት እንዳይራመድ አድርጎት የቆየ አሰራር እንደነበር ጠቅሰዉ የስትራቴጅ እቅዱ ከተቋሙ ዉጭ ባሉ አካላት (በባህር ዳር ዩንቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት) መዘጋጀቱ የከተማዉን ማህበረሰብ ፍላጎትና ችግር በጥናት ላይ ተመስርቶ ምለሽ ለመስጠትና የተቋሙን አላማና ግብ ለማሳካት ከፍተኛ ጥቅም እንደሚኖረዉ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከዚህ በፊት በለጋሽ ድርጅቶችና በሌሎች አካላት ተቋሙ እራሱን የቻለ እስትራቴጅክ እቅድ ሲጠየቅ ባለመኖሩ እርዳታና ድጋፍ ለማግኘት ክፍተት ፈጥሮ ቆይቷል ያሉት አቶ ይርጋ አሁን ላይ የእቅዱ መዘጋጀት ዉኃ አገልግሎቱን በአገር አቀፍም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ ሀገሮች ካሉ የዉኃ አገልግሎቶች ጋር ተወዳዳሪና ተቀራራቢ አገልግሎት ለመስጠት ያስችለዋል ብለዋል፡፡
ስትራቴጅክ እቅዱ የሀገሪቱን ፖሊሲና ስትራቴጅ እንዲሁም አዋጅና ደንቦችን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ በመሆኑ ተቋሙ ምን ቢሰራ የተሻለ ተቋም ሊሆን ይችላል የሚሉ አንኳር ጉዳዮችን በማካተት መሪ እቅዱን መሰረት ያደረጉ ዝርዝር አመታዊ እቅዶችን እያከፋፈሉ በማዘጋጀት ታላላቅና ዘለቄታዊ የዉኃ አቅርቦትና የፍሳሽ ስራዎችን ለመስራት ያስችለናል ሲሉም አብራርተዋል ፡፡ በመሆኑም ስትራቴጅክ እቅዱ ሙያዊ እዉቀትና የካበተ ልምድ ባላቸዉ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጅ ሙህራን እንዲዘጋጅ መደረጉን የተናገሩት ስራ አስኪያጁ ተሳታፊዎቹ በረቂቅ ጥናቱ ላይ የሚካተቱ ሀሳቦችን በማቅረብ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
በመሪ እቅዱ ላይ ከተቋሙ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ካላቸዉ አጋር አካላት ፤ከተቋሙ ማኔጅመንትና ከደንበኞች ፎረም ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ጋር ሶስት ዙር ዉይይት የተካሄደ ሲሆን ዋና ዋና የስትራቴጅክ እቅዱን ክፍሎች ያቀረቡት ደግሞ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኢንስቲትዩት ኦፍ ቴክኖሎጅ ፋካሊቲ መምህራን ዶ/ር ጎጃም አደመና ዶ/ር ትልቅ ጤና ናቸዉ ፡፡
ረቂቅ ጥናቱን መሰረት በማድረግ በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን ከነዚያ መካከል እቅዱን ለመፈፀም ትልቅ በጀት ያስፈልጋል በመሆኑም የበጀት ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች በእቅዱ ተመላክተዋል ወይ ? ድርጅታዊ መዋቅሩ ቅድሚያ ሳይሰጠዉ እቅዱን ማሳካት ይቻላል ወይ ? እቅዱ ከአዲሱ አዋጅ ጋር ቢታረቅ፤ የዉኃ መገኛ ቦታዎችን ዘላቂነት የሚመለከት ጉዳይ በእቅዱ ቢካተት? የከተማዉ የህዘብ ቁጥርን እንደ መነሻ የተጠቀማችሁት የመረጃ ምንጫችሁ ከየት ነዉ ? ወደ ፊትስ ከአስር አመት በኋላ ሊደረስ የሚችለዉን የህዝብ ቁጥር እንዴት መገመት ይቻላል ? ከበጀት አንፃር የከተማ አስተዳደሩ ሚናና ድርሻ ተመላክቷል ወይ ? በከተማ አስተዳደሩ ዙሪያ ያሉ የገጠር ቀበሌዎችና ሳተላይት ከተሞች በክልሉም ሆነ በከተማ አስተዳደሩ በጀት እየተመደበላቸዉ አይደለም ይህ በሆነበት ሁኔታ እቅዱን ማሳካት ይቻላል ወይ ? የሚሉና ሌሎች በርካታ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዋል፡፡ ጥያቄዎችን መሰረት በማድረግም የዉኃ አገልግሎቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ይርጋና ጥናት አቅራቢዎቹ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዉባቸዋል፡፡
ከተሳታፊዎቹ የተነሱ ሀሳቦችን መሰረት በማድረግና ሌሎች ተጨማሪ ጉዳዮችን በቀጣይ ጊዜያትም በጥናቱ በማካተት ስትራቴጅክ እቅዱ ሙሉ ሁኖ ከተዘጋጀ በኋላ የተቋሙ የቀጣይ አስር አመት መሪ እቅድ በመሆን እንደሚያገለግል በፕሮግራሙ ላይ ተገልፃል፡፡

detail

Leave A Comment

Categories

Recent News

Elementor #11675

29 መጋቢ 2025

Elementor #11670

28 መጋቢ 2025

Elementor #11660

28 መጋቢ 2025

Archives