የባህር ዳር ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት
የባህር ዳር ከተማ ውኃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ ስር ላሉ የከተማና የገጠር ነዋሪዎች የመጠጥ ዉኃና የፍሳሽ አገልግሎት ለመስጠት እንዲችል በአንድ ዋና ጽ/ቤት እና በ4 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ተደራጅቶ 408 ቋሚ ሰራተኞችን፣ 73 አውት ሶርስ የጥበቃ ሰራተኞችን እና 70 የቧንቧ ሰራተኛ አጋዥ የቀን ሰራተኞችን በድምሩ 551 የሰዉ ኃይል በማሰማራት ከ28 የውኃ ተቋማት 15 ሚሊዮን ሜ.ኩብ ውኃ በማምረት በ6 የውኃ ማጠራቀሚያና ማሰራጫ ታንከሮች በማሰራጨት በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ 422,969 የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዋች አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ያለ ተቋም ነው።
ራዕይ
ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን ያሟላ የውኃና ፍሳሽ አገልግሎቶች አቅራቢ መሆን
ተልዕኮ
ለባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ህዝብ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ አስተማማኝ፣ ዘላቂና በተመጣጣኝ ዋጋ የውኃና ፍሳሽ አገልግሎቶችን ማቅረብ
የተቋሙ ዋና ዓላማ
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት የተቋቋመበት ዋና ዓላማ በመንግስትም ሆነ በተለያዩ ረጅ ድርጅቶች የተገነቡ የውኃ ወይም የፍሳሽ መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ተረክቦ የማስተዳደር፣ የኦፕሬሽንና የጥገና ሥራዎችን በመስራት ለነዋሪ ማህበረሰብ አስተማማኝ የውኃ የማቅረብና የፍሳሽ አገልግሎቶችን መስጠት ነው።
ዕሴቶችና መርሆዎች
- የከተማዉ ህዝብ የውሃ ሀብት ልማት ተጠቃሚነቱን እናረጋግጣለን፣
- ውሃ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን እናምናለን፣
- የውጤታችን መለኪያ የተገልጋዮቻችን እርካታ መሆኑን እናምናለን፣
- የእኛ ተጠቃሚነት የሚረጋገጠው ኀብረተሰቡ ሲጠቀም መሆኑን እናምናለን፣
- ለከተማ አስተዳደሩ ህዝብ የላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንተጋለን፣
- ግልፅነት፣ ተጠያቂነት፣ ፍትሀዊነት፣ አሳታፊነትና ውጤታማ አሰራር እንከተላለን፣
- ምቹና ሰራተኛው የሚተማመንበት ተመራጭ ተቋም እንፈጥራለን፣
የጽ/ቤቱ የጉዞ ሂደት
የባህርዳር ከተማ ውኃና ፍሳሽ አገልግለት ጽ/ቤት ሶስት የአስተዳደር እርከኖችን እንደተሻገረ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ በእነዚህ ሶስት የዘመናት አስተዳደር እርከኖች የተፈፀሙትን ስንመለከት :-

የቅርብ ጊዜ ታሪክ ከ1995-2015

የመካከለኛ ጊዜ ታሪክ ከ1972-1994

የቀድሞ ጊዜ ታሪክ ከ1952-1971

የቀድሞ ጊዜ ታሪክ ከ1951 ዓ/ም ጀምሮ
የባህር ዳርን ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት በላቀ ደረጃ እየመሩ የሚገኙት ባለራዕይ መሪዎች