የውኃ አገልግሎት
የባህር ዳር ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት በዓመት 23 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ከሦስት ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ምንጮች ማለትም ከጥቁር ውሃ፣ ሎሚ እና አረቄ እና ሰላሳ አራት ጥልቅ ጉድጓዶች ውሃ በማምረት ያቀርባል። አገልግሎቱ በአጠቃላይ 22,075 ሜትር ኩብ መያዝ የሚችሉ 13 የውሃ ማጠራቀሚያዎችን ያሉት ሲሆን ከ600 ኪሎ ሜትር በላይ በሆኑ ዋና የቧንቧ መስመሮች የተጣራ ውሃ ቤት ለቤት ያሰራጫል።
የውኃ አገልግሎቱ ቁልፍ ኃላፊነቶች
- የውሃ ምርት እና ጥራትን ማረጋገጥ
- የውሃ አቅርቦት መሠረተ ልማትን ማስፋፋትና መጠበቅ
- የውኃ ግፊት አስተዳደር ማለትም ፍሳሾችን መቀነስ እና ስርጭትን ፍትሐዊ ማድረግ
- ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የውኃ ተደራሽነት ማሻሻል